ወንጀለኛው


ነገሩ እንዲህ ነው አንድ የታወቀ ወንጀለኛ በስንት መከራ ተያዘ። ተይዞ ፖሊስ መረመረው። በተያዘ በሳምንቱ በጠና ታሞ ሆስፒታል ይሄዳል። ታዲያ ዶክተሩ "ትርፍ አንጀት ስለሆነ ትርፍ አንጀቱ ተቆርጦ መውጣት አለበት" ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወጣለት።

እንደገና በሳምንቱ ታመመ ዶክተሩ "ጉበቱ ግማሹ ስለተጎዳ ተቆርጦ መውጣት አለበት" ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወጣለት።
እንደገና አሁንም በሳምንቱ ታመመና ሆስፒታል ሄደ።
ዶክተሩ "አንዱ ኩላሊት ስራውን ስላቆመ መውጣት አለበት" ሲል ወንጀለኛውን ሲያመላልስ የነበረው ፖሊስ ወደ ዶክተሩ ጠጋ ብሎ እኔ ምልህ ዶክተር "ይህ ሰው ዘመድህ ነው እንዴ"? ይለዋል።
ዶክተሩም "ኧረ ዘመዴ አይደለም። ምነው?" ሲለው ፖሊሱ ምን ቢል ጥሩ ነው?

"ቀስ በቀስ ከእስር ቤት እያወጣሀው እኮነው። እንደመኪና መለዋወጫ አካሉን ቀስ በቀስ እየከፋፈልክ ከእስር ቤት አስወጥተህ መልሰህ ልትገጣጥመው ይሆናላ
"

src:ይርዳው ጤናው

Comments

Popular Posts